ምርምርና ልማት ማዕከል

በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ስራ የተጀመረው ኤች.. በተባለ የደች ኩባንያ ... 1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡

ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር ... 1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ስልጠና መስጠት እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋምም ለምርምርና ስልጠና ተግባራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሥራው በዘርፍ ደረጃ እንዲመራ ተወስኖ 2003. ጀምሮ የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

  • ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied research) በማካሄድ ለኮሜርሽያል አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ፤
  • ምርታማነትን በማሳደግ ምርትን መጨመርና ወጪን መቀነስ፤
  • የአመራረት ቅልጥፍናን ለማሻሻል የተገኘውን የምርምር ውጤት በእያንዳንዱ ስኳር ፋብሪካና ማሳ ላይ በአግባቡ እንዲውል ማስረጽ፤
  • በአመራረት ሥርአት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎች (optimization) እንዲወሰዱ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት መስጠት፤
  • ስራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ለኢንዱስትሪው ያስገኙትን ፋይዳ እና በአካባቢው ላይ ያደረሱትን ተጽዕኖ መገምገምና አዳዲስ የምርምር አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍ፤
  • ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ፣ በሽታ የሚቋቋሙ፣ ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውና ቶሎ የሚደርሱ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችን እንዲሁም የተሻሻሉ የሸንኮራ አገዳና የስኳር አመራራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎችን ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ማስተዋወቅና በስራ ላይ ማዋል፤
  • በኦፕሬሽን ላይ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ደረጃቸው (ስታንዳርድ) ሳይጓደል ትግበራቸው የሚቀጥልበትን አሰራር መቀየስ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስተግበር፤

ኢንዱስትሪውን በሰለጠነና ውጤታማ በሆነ የሰው ኃይል ለመደገፍ ሥልጠናዎችን በማመቻቸትና በማሰልጠን ቁልፍ ሚና መጫወት፡፡

ከአዲስ አበባ 110 . ርቀት ወንጂ ላይ የሚገኘው የምርምርና ልማት ማዕከል እነዚህን ተግባራት በብቃት ለመወጣት 2008. በአዲስ መልክ ተደራጅቷል፡፡

ማዕከሉ በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ተንዳሆ፣ አርጆ ዲዴሳ እና ከሰም ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም በጣና በለስ፣ ኦሞ ኩራዝ እና ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የምርምር ጣቢያዎችን አቋቁሞ የሸንኮራ አገዳ፣ የዝርያ ልማት እና የስኳር ቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

Top