ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ

aiየሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦ ካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህን ኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱን ለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡

በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚ አየር ንብረት፣ በመሰኖ ሊለማ የሚችል ሰፊ የእርሻ መሬት (500 ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግሥት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋና መተሓራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪ በተለይም 2003. ወዲህ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡

በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት ይህ ኢንዱስትሪ ስኳር ከማምረት ጎን ለጎን ተረፈ ምርቶቹን ለሃይል ማመንጫ (ከባጋስ) ለእንስሳት መኖ (ከሞላሰስ) ለነዳጅ (ከፓወር አልክሆል፤ ኤታኖልን ከቤንዝል ጋር በማደባለቅ) ለማዳበሪያ (ከፊልተር ኬክና ቪናስ) ለወረቀት መስሪያ (ከባጋስ) ለህክምና (ከቴክኒካል አልክሆል) ለአልክሆል መጠጥ (ከሬክቲፋይድ አልክሆል) ለቀለም መስሪያ (ከሞላሰስ) ለብርጭቆ መስሪያ (ከቦይለር አሽ) ወዘተ አገልግሎቶች ያውላል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የስኳር ፍላጎት የደረሰበት ደረጃ ሲታይ የዛሬ 62 ዓመት ገደማ በላንድሮቨር መኪና በየገበያው በመዘዋወር ስኳርን ለማስተዋወቅ ብርቱ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ማመን ይከብዳል፡፡ በወቅቱ ሻይ ቅመሱልኝበነጻ በመጋበዝ ሕዝቡን ከምርቱ ጋር ለማላመድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከብዙ ጥረት በኋላ ውጤት ማስገኘት ችሏል፡፡

በዚህ ሁኔታ የተጀመረው የስኳር ትውውቅ ዛሬ ላይ ታሪኩን በመቀየር ሀገሪቱ እያስመዘገበች ካለችው ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ በጣም ተፈላጊ ምርት ሆኗል፡፡

በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት 1943. አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946. ስራ አስጀምሯል፡፡

woበመቀጠልም 1955. እዛው ወንጂ ላይ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንጂና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ በእርጅና ምክንያት እንደ ቅደም ተከተላቸው 2004. እና 2005. መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ 2006. ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል።

በኢትዮጵያ የስኳር አዋጭነትን የተረዳው የሆላንዱ ኩባንያ በተመሳሳይ የመተሓራ ስኳር ፋብሪካን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርቲ ከተማ ሰኔ 26 ቀን 1957. በአክሲዮን መልክ በመመስረት 1962. ፋብሪካውን ሥራ አስጀመረ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በፊንጫአ ሸለቆ 1967. በተካሄደ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አካባቢው ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተገንብቶ 1991. ማምረት ጀመረ፡፡

ሀገሪቱ ለስኳር ልማት ያላትን ምቹ ሁኔታ የተረዳው የኢፌዲሪ መንግሥት ልማቱን ለማስፋፋት በማቀድ በአፋር ክልል በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ያለውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 አቋቋመ፡፡ ፋብሪካው 50 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀም ሲሆን፣ በዓመት 6 ሚሊዮን 190 ኩንታል ስኳር እና 63 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል እንዲያመርት ታቅዶ የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት አምርቷል፡፡

ምንም እንኳ የስኳር ኢንዱስትሪው ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም፤ የስኳር ልማቱ በሚፈልገው ፍጥነት አለማደግ፣ ሀገሪቱ በተከታታይ እያስመዘገበች ካለቸው ፈጣን የኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣት፣ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የሚያመርቱት የስኳር መጠን እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ማርካት አለመቻል፣ የሕዝብ ቄጥር ማደግ እና ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ከመስፋፋት ጋር ተያይዞ የስኳር ፍላጎትና አቅርቦት ሊጣጣም አልቻለም፡፡

ከዚህ አንጻር መንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም በየአመቱ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ ሀገር እያስገባ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ክፍተቱን ለመሙላት ስኳር ከውጭ መግዛት ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑና በዚህ ሁኔታም መቀጠል ስለማይቻል ከመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አንስቶ በሀገራችን ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንዱ የስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሊሆን ችሏል፡፡

ttመንግሥት የስኳር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም ከሚያደርገው ርብርብ ባሻገር በዘርፉ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ በተለይም በልማቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ለማስገኘት ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካን ከመገንባት አንስቶየስኳር አብዮትበሚያስብል ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች ከፍተኛ መዋለ ነዋይ የወጣባቸውን መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የወንጂ ሸዋና የፊንጫኣ ነባር ስኳር ፋብሪካዎችን በማዘመን የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ተችሏል፡፡ በማስፋፊያ ሥራዎች አማካይነትም ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠንን 2002. መጨረሻ ከነበረበት 2 ሚሊዮን 903 740 ኩንታል በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (2007.) ወደ 4 ሚሊዮን ኩንታል አድጓል፡፡

በሌላ በኩል የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ ሥራ ማስጀመር የተቻለውም በዚሁ የመጀመሪያ እቅድ ዘመን ነበር፡፡ ምንም እንኳ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ፋብሪካውን ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ውስጥ ማስገባት ባይቻልም የሙከራ ምርት ለማስጀመር ግን ተችሏል፡፡ በቀጣይም ፋብሪካውን ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ለማስገባት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

የአገዳ ልማትን በተመለከተም በዕቅድ ዘመኑ ተጨማሪ 65 363 ሄክታር መሬት በአገዳ ለምቷል፡፡ ይህም በእቅዱ መነሻ ከነበረው 30 397 ሄክታር ጋር ሲነጻጸር 215 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የኤታኖል የምርት መጠንም 2002. ከነበረበት 7 ሚሊዮን 117 ሊትር በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ወደ 19 ሚሊዮን 804 ሊትር ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 18 ሚሊዮን 480 ሊትር ከቤንዝል ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ እንዲሁም በሃይል ማመንጨት ረገድ የወንጂ ሸዋና ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ካመነጩት ሃይል ውስጥ ለራሳቸው የሚያስፈልጋቸውን ሃይል ተጠቅመው የተረፋቸውን 31 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ብሔራዊ የሃይል ቋት ማስገባት ጀምረዋል፡፡

tcየአገዳ ምርታማነትን ያሳደጉ በርካታ የምርምር ሥራዎችም የተከናወኑ ሲሆን፣ የጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) እና የውሃ መቀልበሻ (ዊር) የሰፋፊ መስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የቤቶች እና የግዙፍ አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተካሂደዋል፡፡ ልማቱን ተከትሎም አነስተኛ ከተሞችና በርካታ መንደሮች ተመስርተዋል፡፡

በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ረገድም በርካታ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ ወፍጮ ወዘተ) እና የመሰረተ ልማት አውታሮች (ንጹህ መጠጥ ውሃ፣ መንገድ ወዘተ) ተገንብተው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተጠቃሚ በመሆን የኑሮ ደረጃቸው መሻሻል ጀምሯል፡፡ እንዲሁም ለአካባቢው ተወላጆች ልጆች ቅድሚያ በመስጠትና በትራክተር ኦፕሬተርነት፣ በግምበኛነት፣ በአናጺነት፣ በጥበቃና በመሳሰሉት ሙያዎች በማሰልጠን በየፕሮጀክቶቹ ተመድበው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡

የአካባቢው ወጣቶችም በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው በልማቱ ስራ ውስጥ እንዲሳተፉና ገቢ እንዲያገኙ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በመስኖ የለማ መሬት ለአካባቢው ነዋሪዎች አመቻችቶ በማስረከብ በተለይም በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አካባቢ የሚገኘው ማህበረሰብ እንደ በቆሎ የመሳሰሉ ሰብሎችን አምርቶ እንዲጠቀምና በቀጣይም በዘላቂነት ሸንኮራ አገዳ አልምቶ ለፋብሪካ እንዲያቀርብ ለማስቻል በወንጂ አካባቢ አገዳ ከሚያበቅሉ አርሶ አደሮች (አውት ግሮወርስ) ልምድ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

በስራ ዕድል ፈጠራም ባለፉት አምስት ዓመታት በስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች 350 በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች በዘርፉ የታቀደውን ያህል ውጤት ማግኘት ባይቻልም እንኳ፣ በስኳር ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ በተከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሀገሪቱ 2016. በዓለም ላይ ከሚገኙ 10 ከፍተኛ የስኳር አምራች ሀገሮች ተርታ መሰለፍ የምትችልበትን እድል እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መደላድሎችን ለመፍጠር ተችሏል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመንም ተንዳሆን ጨምሮ በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ ስምንት አዳዲስ ፋብሪካዎችን ማለትም የኦሞ ኩራዝ 1 2 3 እና 4 የጣና በለስ 1 እና 2 እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ፋብሪካዎችን ግንባታ አጠናቆ ስራ ለማስጀመር ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በማጠናቀቂያ ምእራፍ ላይ ይገኛል፡፡

በእነዚህ መጠነ ሰፊ ሥራዎች አመታዊ የስኳር መጠንን በማሳደግ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማርካት ባሻገር ምርቱን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ታቅዷል፡፡ የሸንኮራ አገዳ ልማትን ከማስፋፋት አኳያም በዕቅድ ዘመኑ 211 564 / በመትከል 2012. መጨረሻ በአገዳ የተሸፈነውን መሬት 307 324 ሄክታር ለማድረስ ነው የታቀደው፡፡

tbበተጨማሪም በኤታኖል ምርት፣ በሃይል አቅርቦት፣ በመስኖ መሰረተ ልማትና በቤቶች ግንባታ ረገድ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመስራት ታቅዷል፡፡ የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ከማሳደግ አኳያም በእቅድ ዘመኑ ልማቱ በሚፈጥረው የስራ ዕድል በቋሚነት፣ በጊዜያዊነት፣ በኮንትራትና በማህበራት 637 በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡

በአጠቃላይ ጥቅምት 2003. ተቋቁሞ የዘርፉን ልማት እየመራ የሚገኘው የስኳር ኮርፖሬሽን የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የስኳር ልማቱ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቦችን የልማት ተጠቃሚ በማድረግ፣ የተለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮችና ማህበራዊ ተቋማትን በመገንባት፣ መጠነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ ልማት በማካሄድና ከፍተኛ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ማረጋገጡን ማየት ቢቻልም፤ የፋብሪካ ቁጥር፣ ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶችን በማሳደግ ረገድ ገና ብዙ ሥራ መስራት እንደሚገባ መገንዘብ ተችሏል፡፡

ከዚህ አንጻር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ኮርፖሬሽኑ የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ለውጦችን ማድረግ እንዳለበት በመንግሥት ታምኖበታል፡፡ ከእነዚህ ለውጦች መካከል ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስችል አዲስ አደረጃጀት መፍጠር አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ኮርፖሬሽኑ የስኳር ልማትን በሀገሪቱ በስፋት ለማካሄድ በሚያስችል በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

Top