ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

wolkit

ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 1 300 . ርቀት ላይ በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቱ 50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው የስኳር ፋብሪካ ይገነባል፡፡ በዚህ መሰረት CAMC ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የኮንትራት ውል ተገብቶ ስራው በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ግንባታው ተጠናቆ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840 ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡

ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው የመስኖ ውሃ አቅርቦት ዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ከሚገኘው የሜይ-ዴይ ግድብ የሚገኝ ሲሆን፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ 840 ሜትር ስፋት እና 135.5 ሜትር ቁመት ይኖረዋል፡፡

የመስኖ መሠረተ ልማት

  • 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም የሚኖረው የዛሬማ ግድብ ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፤
  • ከግድብ ግንባታው ጎን ለጎን በጠብታ መስኖ 7ሺህ / መሬት ለማልማት NETAFIM ከተባለ የእስራኤል ኩባንያ የመስኖ መሠረተ ልማት ሥራ ተቋራጭ ጋር ውል ተገብቶ ሥራው ተጀምሯል፤
  • 10 /ሜትር የዋና ቦይ (Main canal) ግንባታ ተጠናቋል፤
  • 3ሺህ / መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን፣ የመስኖ ውሃው እስከሚደርስ ድረስ የጥጥ ልማት እየተካሄደ ነው፤
  • 261 ሄክታር መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤

የአገዳ ልማት

  • 220 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤

የቤቶች ግንባታ

  • 800 መኖሪያ ቤቶች እና 36 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮችተገንብተዋል፤

Top