በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

belescon

ከአዲስ አበባ 576 . ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በዋናነት የሚገኘው በአማራ ክልል ሲሆን፣ የተወሰነ የአገዳ እርሻ ልማቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካተት ነው፡፡

በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች እየተገነቡ  ሲሆን፣ 50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው የመስኖ ውሃ የሚገኘው በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውሃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡

ፋብሪካዎቹ ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 2 ሚሊዮን 420ሺህ ኩንታል ስኳር እና 20 ሚሊዮን 827ሺህ ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በመገንባት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ፋብሪካዎች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ግንባታቸው ተጠናቆ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ

  • በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ የሚገኘው የጣና በለስ-1 ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤

የመስኖ መሠረተ ልማት

  • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 30 / ርዝመት ያለውና 60 / ውሃ በሰከንድ ማስተላለፍ የሚችል የወንዝ መቀልበሻ፣ መቆጣጠሪያ፣ የደለል ማስወገጃ እና የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤
  • 12 ሺህ 807 / መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤

የአገዳ ልማት

  • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 13ሺህ 49 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤

የቤቶች ግንባታ

  • በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 1ሺህ 945 መኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮች) ተገንብተዋል፤

ጣና በለስ-2 ስኳር ፋብሪካ

  • በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) እየተገነባ የሚገኘው የጣና በለስ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፤
Top