የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት

IMG 2196

ከአዲስ አበባ 250 .ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 . ያህል የሚርቀው ይህ ፋብሪካ፣ በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካኝነት 20ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡ የአገዳ ልማቱም የሚከናወነው በከሰም እና ቦልሀሞን በተሰኙ አካባቢዎች ነው፡፡

የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡

ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ፣ 2007. መጨረሻ ላይ የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ አሁን ስኳር እያመረተ ሲሆን፣ በሂደት በቀን 6ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይም 10ሺህ ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፣ የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡

ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ 1 ሚሊዮን 530ሺህ ኩንታል ስኳር እና 12 ሚሊዮን 500ሺህ ሊትር ኢታኖል በዓመት የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ ደግሞ በዓመት 2 ሚሊዮን 600ሺህ ኩንታል ስኳር እና 30 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 15 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ

  • 2ሺህ 946 / መሬት ውሃ ገብ ተደርጓል፤

  • 20.5 . የዋና ቦይ ግንባታ ተጠናቋል፤

የአገዳ ልማት

  • በፋብሪካው አማካኝነት 2ሺህ 413 ሄክታር መሬት እንዲሁም በአሚባራ እርሻ ልማት (አውት ግሮወር) 6ሺህ ሄክታር መሬት በአጠቃላይ 8 ሺህ 443 ሄክታር በአገዳ ተሸፍኗል፤

የቤቶች ግንባታ

  • 517 የመኖሪያ ቤቶች እና 20 አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮችተገንብተዋል፤

Top