አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ፣ በኢሉ አባቦራና በጅማ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ - ጅማ -በደሌ - ነቀምቴ መስመር 540 . ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በሦስቱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 49 ቀበሌዎችን የሚያካትት ነው፡፡

የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ ደግሞ 1400 ሚሊ ሜትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ስርጭቱም ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

AL-Habasha Sugar Mills PLC ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ 2005. ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ይዞታነት የተሸጋገረው ይህ ፋብሪካ በሂደት 20 ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

ፕሮጀክቱ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው የግንባታ ስራ 90 በመቶ በላይ ተጠናቆ የነበረ ሲሆን፣ 2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የስራ አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል፡፡

ፋብሪካው በግብአትነት የሚጠቀምበትን ሸንኮራ አገዳ ለማልማት ውሃ ከዲዴሳ ወንዝ የሚያገኝ ሲሆን፣ ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ራሱን ከመቻል አልፎ ቀሪውን ለብሔራዊ የኃይል ቋት እንደሚያበረክት  ይጠበቃል፡፡  ከፍተኛ የኤታኖል ምርት የማምረት አቅምም አለው፡፡

ፋብሪካው ግንቦት 6 ቀን 2007. በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡

 የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ

  • 1 660 / መሬት  ውሃ ገብ ተደርጓል

የአገዳ ልማት

  • 3ሺህ 448 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤

የቤቶች ግንባታ

  • 64 የመኖሪያ ቤቶች እና ሁለት አገልግሎት መስጫ ተቋማት (ብሎኮችተገንብተዋል፤

Top