ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

Tendaho Sugar Factoryjpg

በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛው አካባቢ በአፋር ክልል 50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተምስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ 300 . ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

1998. የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ግንባታው OIA (Overseas Infrastructure Alliance) በተባለ የህንድ ኩባንያ የሚካሄደው ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥቅምት 2007. የሙከራ ምርት ጀምሮ በአሁኑ ወቅት በመደበኛ የምርት ሂደት ውስጥ ይገኛል፡፡

ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በቀን 13ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡

በተጨማሪም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከሚያመነጨው 60 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 38 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኃይል ቋት በማስገባት እንዲሁም 31 ሚሊዮን ሊትር ያህል ኤታኖል በማምረት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለፋብሪካው በግብዓትነት ከሚያስፈልገው 50ሺህ ሄክታር መሬት ከሚለማ የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 25ሺህ ሄክታሩ የሚለማው በፋብሪካው ሲሆን፣ ቀሪው 25ሺህ ሄክታር መሬት ደግሞ በአካባቢው በሚገኙ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮች የሚለማ ነው፡፡ የአገዳ ልማቱ በመከናወን ላይ የሚገኘው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው የተንዳሆ ግድብ አማካኝነት ሲሆን፣ 1.86 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ 60ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚያለማ ይጠበቃል፡፡

ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመቻቸቱም አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡

የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ

  • በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ 22 ሺህ 835 / መሬት ውሃ ገብ ሆኗል፤
  • 42 / በላይ የዋና ቦይና ተያያዥ ስትራክቸሮች ግንባታ ተከናውኗል፤

የአገዳ ልማት

  • በመጀመሪያው ዙር 20 ሺህ 866 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፤

የቤቶች ግንባታ

  • 175 የመኖሪያ ቤቶች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 429 ሕንጻዎች (ብሎኮችተገንብተዋል፤
Top