በማቋቋሚያ አዋጅ ደንብ ቁጥር 192/2003 መሰረት የስኳር ኮርፖሬሽን ዓላማ

 • የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣
 • ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን በፋብሪካ ማዘጋጀትና ማምረት፣
 • ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣
 • አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ስራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣
 • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን በስራ ላይ ማዋል፣
 • አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬሽን ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፣
 • በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣
 • የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን ማበረታታትና መደገፍ፣
 • ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር፣
 • የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፣
 • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መስራት ናቸው፡፡
Top